በቅዱስ አማኑኤል የአእምሮ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል የአእምሮ ጤና ሀኪሞች ሀሳብ አመንጪነት ፤ ድርጅታችን ዳጉ ኮሚንኬሽን ሃላ/የተ/የግ/ማህበር ከቅዱስ አማኑኤል የአእምሮ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል እና ልዩ ልዩ ባለድርሻ አካላት ጋር በመተባበር በሆስፒታሉ ቅጥር ግቢ ውስጥ ” እፎይታ የመዝናኛና የአእምሮ ህመም ግንዛቤ ማስጨበጫ ሳምታዊ የኪነ ጥበብ ፕሮግራም ” ፕሮግራሙ ሁልጊዜ ቅዳሜ 8 ሰዓት ላይ ይካሄዳል ።

በፕሮግራሙ ላይ የሆስፒታሉ የማህበረሰብ አባላትና ጥሪ የተደረገላቸው የክብር እንግዶች የሚገኙ ሲሆን ልዩ ልዩ የኪነ ጥበብ ስራዎች ይቀርባሉ። የምትችሉ ዝግጅቱ ላይ እንድትታደሙ እንዲሁም የአእምሮ ጤና የበጎ ፈቃድ አምባሳደር እንድትሆኑ በታላቅ አክብሮት ተጋብዛችሁዋል።

Language/ቋንቋ