የአዕምሮ ጤና ምንድን ነው?

የአዕምሮ ጤና ምንድን ነው?

የአእምሮ ጤና ማለት የአእምሮ እክል አለመኖር ብቻ አይደለም፡፡ የአለም ጤና ድርጅት እንደሚለው ጤና ማለት በአካል ፣ በአዕምሮ እና ማህበራዊ ደህንነቱ የተሟላ መሆን እንጂ የበሽታ አለመኖርን ብቻ አያመለክትም፡፡የአዕምሮ ጤና ጽንሠ ሀሳብ በራስ ማንነት ላይ ያተኮረ(ግላዊ) ደህንነት፤ ግለሰባዊ አቅም ፤ ራስን የመቻል፤ ብቃት፤ ግለሠባዊ እውቀቱን እና ስሜቱን ተረድቶ ተግባራዊ የማድረግ ችሎታን ያካትታል፡፡ እንዲሁም ሌሎች ግለሠቦች ችሎታውን/ዋን ሊረዱት፤ ሊያውቁት እና ሊገነዘቡት የሚችል የመደበኛው የህይወት ጉዞን የተከተለ ÷ ምርታማና ውጤታማ ስራን የሚሰራ እና ለሚኖርበት ማህበረሰብ አስተዋፅኦ ማድረግ የሚችል የአእምሮ ጤና ደህንነት ፅንሠ ሀሳብ በሚል ይቀመጣል፡፡የአዕምሮ ጤና ችግር አንድን አነስተኛ ወይም የተለየን ቡድን ወይም ማህበረሰብ የሚጎዳ ሳይሆን ሁሉንም ማህበረሰብ ክፍል የችግሩ ተጠቂ የሚያደርግ ነው፡፡ በዚህም ለአለማችን እድገት ትልቅ ፈተና ነው፡፡ ማንም ቡድን ወይም ግለሠብ በተፈጥሮው የአዕምሮ እክልን የመከላከል አቅም የለውም ነገር ግን በድህነት ያሉ፣መኖሪያ አልባዎች ፣ሥራ አጦች ያልተማሩ፣የግጭት ሰለባ የሆኑ ፣ ስደተኞች፣ህፃናት እና ወጣቶች ፣ ጥቃት የደረሰባቸው ሴቶች እና ሞግዚት አልባ አረጋውያን ላይ የበለጠ የአዕምሮ እክል አደጋው ከፍተኛ ነው፡፡• የአዕምሮ፤ የአካል እና የማህበራዊ ጤና ለሁሉም ሰው በጥብቅ የተቆራኙ ዋና የህይወት መሠናስሎች(strands) ናቸው፡፡- ዛሬ ላይ የአዕምሮ ጤና ችግር ስፋት እና ጫናን ስንመለከት እስከ 970 ሚሊዮን የሚደርስ ህዝብ በአዕምሮ ህመም ይሰቃያል፡፡ እንዲሁም በየአመቱ ወደ 1 ሚሊዮን የሚሆኑ ሰዎች ራሳቸውን በራሳቸው ያጠፋሉ፡፡- በአንድ ቤተሰብ ውስጥ ካሉ 4 ሠዎች ውስጥ ቢያንስ 1 ሠው በህይወቱ የአዕምሮ ህመም እንደሚጋጥመውም ጥናቶች ያመላክታሉ፡፡በሌላ በኩል የአዕምሮ ህመም ተጠቂዎች ተጋላጭነታቸው የህክምና አገልግሎትን ካለማግኘት ባሻገር ሠብአዊ መብታቸው ያለመከበር እና አድሎና መገለል በአዕምሮ ህክምና መስጫ ተቋማት ሣይቀር በውስጥም በውጭም ይደርስባቸዋል፡፡ ሡስ አስያዥ ንጥረ ነገሮች የሚያስከትሉት ጫና ዓለማቀፋዊ አሃዞች- በአለም ላይ 76.3 ሚሊዮን ሰዎች አብዝተው አልኮልን የሚጠቀሙ እንደሆነ በምርመራ ተረጋግጧል፡፡- በትንሹ 15.3 ሚሊዮን የሚደርሱ ሠዎች ከሱስ አስያዥ ንጥረ ነገሮችን ከመጠቀም ጋር ተያይዞ የአዕምሮ እክል ይገጥማቸዋል፡፡- አሁን ላይ ከ 5 እስከ 10 ሚሊዮን የሚደርሱ ሰዎች ሱስ አስያዥ ንጥረ ነገሮችን በመርፌ የሚወስዱ መሆናቸው ጥናቶች ያረጋግጣሉ፡፡በአለም ላይ ከ 5 -10% የሚደርሱ አዲስ የኤች አይ ቪ ተጠቂዎች ሡስ አስያዥ ንጥረ ነገሮችን በመርፌ የሚወስዱ እንደሆነም ተረጋግጧል፡፡- እ.ኤ.አ በ2000 በአለም ላይ የተመዘገበው 205,000 የሞቱ ሠዎች በድብቅ/በህገወጥ መንገድ ሡስ አስያዥ መድሀኒቶችን የሚጠቀሙ ናቸው፡፡- የአልኮልና የሌሎች ሡስ አስያዥ ንጥረ ነገሮች ተጠቂ መሆን በሁሉም በአደጉና ባላደጉ ሃገሮች ላይ ትልቅ የማህበረሰብ የጤና ጠንቅ ሆኖ የቀጠለ ነው፡፡ስለአዕምሮ ህመም መነጋገር ስለድህነት መወያየት ነው፡ ሁለቱም የአንድ ሳንቲም ሁለት ገፅታዎች ናቸው፡፡- የአዕምሮ ህመም ህክምና ከሚወስደው ረጅም የህክምና ጊዜ፤ የገንዘብ ወጪ እና በዚህ ወቅት ለሚያጋጥመው የምርታማነት ማሽቆልቆል የአዕምሮ ህመም ለድህነት መፈጠር ከፍተኛ አስተዋፅኦ እንደሚያደርግ ባለሙያዎች ይሞግታሉ፡፡ በተመሳሳይ የደህንነት አለመጠበቅ፣ ዝቅተኛ የትምህርት ደረጃ፣ በቂ መኖሪያና የተመጣጠነ ምግብ አለመኖር ሁሉም በአብዛኛው ለሚከሠተው የአዕምሮ ህመም መፈጠር አስተዋፅኦ ያደርጋሉ፡፡ ሣይንሳዊ ግኝቶች እንደሚያመለክቱት ከሆነ ከ 1.5 እስከ 2 ጊዜ በላይ አነስተኛ ገቢ ያላቸው ሠዎች ለድብርት ህመም ይበልጥ ተጋላጭ እንደሆኑ ነው ፡፡ በዚህም ድህነት ለአዕምሮ ህመም መከሰት አስተዋፅኦ ያለው መሆኑና በሌላ ጎኑም የአዕምሮ እክል ለድህነት መከሰት አስተዋፅኦ የሚያደርግ እንደሆነ ያሳያል፡፡ ሥራ- ሥራአጥ እና ስራ ለመቀጠር ያልቻሉ ሰዎች ስራ ካላቸው ሰዎች የበለጠ የድብርት ምልክቶች ይታዩባቸዋል፡፡ በተጨማሪም ጥናቶች እንደሚያመላክቱት ከስራ የተሰናበቱ (ስራቸውን ያጡ) ሰዎች በስራ ላይ ከሚገኙ ሰዎች 2 እጥፍ በበለጠ የድብርት ህመም ይስተዋልባቸዋልትምህርት- በሌላ በኩል በአብዛኛው በሚከሰቱት የአዕምሮ ህመሞች ሥርጭትና በዝቅተኛ የትምህርት ደረጃ መካከል ትልቅ የሆኑ ግንኙነት እንዳለ ይገልፃሉ፡፡ በተጨማሪም ዝቅተኛ የትምህርት ደረጃ መኖር ከፍተኛ የሥራ መስክ ላይ ለመሠማራት እድሉን በመንፈግ እክሉ እንዲፈጠር ተጋላጭነትን በመጨመር ÷ የደህንነት እጦትንና ቀጣይነት ያለው ዝቅተኛ ለሆነ ለማህበራዊ-ኢኮኖሚ አስተዋፅኦ ያደርጋል፡፡ በዚህም ማሀይምነትና ህመም የድህነት ቁልፍ ናቸው፡፡ግጭት እና ጉዳት- በድህነት በተጠቃ ማህበረሰብ ውስጥ ግጭት እና ጥቃት መድረሱ የተለመደ ነው፡፡ እነዚህም በአጠቃላይ የአዕምሮ ደህንነትን በመጉዳት ለአዕምሮ ህመሞች ይበልጥ ተጋላጭ ያደርጋሉ፡፡ በአዕምሮ ጤና ክብካቤ ላይ በደንብ የተዋቀረና የታለመ የመዋዕለ ንዋይ ፍሰት ከሌለ የድህነትና የአዕምሮ እክል ትስስራዊ ዑደት ይቀጥላል፡፡ ለአዕምሮ ጤና ክብካቤ ተደራሽ ያለመሆን እንቅፋቶች# አድሎ ማድረግበአለም ላይ ከአዕምሮ ህመም ጋር የሚኖሩ ብዙ ሠዎች በህመማቸው ምክንያት ተጎጂዎችና ፍትሀዊ ላልሆነ መገለል ኢላማ ይደረጋሉ፡፡በተጨማሪም የመኖሪያ፣የስራ እንዲሁም ነባራዊ የሆኑ ማህበራዊ ምቹ ሁኔታዎች ተደራሽነትንም ይነፈጋሉ፡፡#ከአዕምሮ ጤና ክብካቤ ኢንሹራንስ ሽፋን መገለል በብዙ አገራት የአዕምሮ እክል ህክምና በጤና ኢንሹራንስ ማዕቀፍ ባለመሸፈኑ ምክንያት ብዙዎቹ ህክምናቸውን መሸፈን አይችሉም ለአብነትም 1/3ኛ ማለትም 2 ቢሊዮን የሚሆነው የአለም ህዝብ የሚኖረው የአዕምሮ ጤና በጀት ከአጠቃላይ የጤና በጀታቸው ላይ ከ 1% በታች በመደቡ ሀገራት ውስጥ ነው፡፡# የመድሀኒት እጥረትበአብዛኛው 20% የሚሆኑ ሀገራት ቢያንስ አንድ እንኳ የድብርት ፣ የሳይኮሲሰና ለሚጥል ህመም የሚሆን መድሀኒት በመጀመሪያ ደረጃ ጤና አጠባበቅ ላይ እንደሌላቸው ጥናቶች ያመለክታሉ፡፡# የቅደም ተከተል ችግርበጣም ብዙ ሃገሮች በተለይም ያደጉ ሃገሮች ብዙውን ሃብታቸውን የሚያጠፉት በብዛት ለአዕምሮ ምቹ ስፍራን በመፍጠር ላይ ሲሆን ለሠብአዊነትና ለህክምናው ግን ዝቅተኛና ደካማ የሆነ የክብካቤና የሃብት አጠቃቀም እንዳላቸው ይስተዋላል፡፡#በመጀመሪያ ደረጃ የጤና አጠባበቅ ላይ ያለ የክህሎት እጥረት የአዕምሮ እክልን እንዴት በአግባቡ መለየትና ህክምና መስጠት እንደሚቻል የሚያውቁ በጣም ጥቂት ሀኪሞችና ነርሶች መሆኑ እንዲሁም41% በሚሆኑ ሀገራት ውስጥ ለመጀመሪያ ደረጃ የጤና አጠባበቅ ባለሙያዎች የአዕምሮ ጤና ሥልጠና ፕሮግራም የሌላቸው መሆኑን ጥናቶች ይፋ አድርገዋል፡፡# ፍትሃዊና ሁሉን አቀፍ የሆነ የአዕምሮ ጤና ፖሊሲና የህግ ማእቀፍ አለመኖር- በአለም ላይ 40% የሚሆኑ ሀገራት የአዕምሮ ጤና ፖሊሲ የላቸውም እንዲሁም 20% የሚሆኑት ሀገራት ደግሞ የአዕምሮ ጤና የህግ ማእቀፍ የላቸውም፡፡ በሌላ በኩል ደግሞ 30% የሚሆኑ ሀገራት ብሄራዊ የአዕምሮ ጤና ፕሮግራም እንደሌላቸው የአለም አቀፍ ጤና ድርጅት(2000) ጥናት ያመላክታል፡፡ በአጠቃላይ 13% የሚሆነው የዓለም ህዝብ በአዕምሮ ጤና እክል እና በሱስ አስያዥ ንፅረ ነገሮችን በመጠቀም ይጠቃል፡፡ የአዕምሮ ህመም ከምንላቸው መካከል ጥቂቶች• ጭንቀት፤ ተገቢ ባልሆነ ሁኔታ ወይም ከተገቢው መጠን በላይ የሆነ የፍርሀት አይነት ሥሜት ሲሆን ለህልውና ምንም ጠቀሜታ የሌለው ነው፡፡• ድብርት (ድባቴ)፤ ቀጣይነት ያለው የሥሜት መዋዠቅ፤ ድካም እና ከፍተኛ ሃዘን መሰማት ዋነኛ ምልክቶች ናቸው፡፡• የአደንዛዥ ዕፅ ሡሥ፤ በተከታታይ አልኮልን ወይም አነቃቂ መድሃኒቶችን በሠውየው የቀን ባህሪ ላይ ጣልቃ በመግባት ባህሪን ሊቀይሩ የሚችሉትን አብዝቶ መጠቀም ነው፡፡ ይህም ማለት አንድ ሠው ራሱን መቆጣጠር እስኪያቅተው ድረስ የሱስ አምጭ ንጥረ ነገሮችን ለመውሰድ ፍላጎት ሲያደርበትና ችግር የሚያስከትሉ እንደሆነ እያወቀ እነዚህን ንጥረ ነገሮች ሲወስድ ነው፡፡• ባይፖላር፤ በሁለት የተለያዩ የስሜት ፅንፎች ግለሰቡ እንዲገኝ የሚያደርግ ሲሆን ከመጠን ባለፈ የደስታ ሥሜት ውስጥ መገኘት በሌላ በኩል ደግሞ ከመጠን ባለፉ የድብርት ሥሜት ውስጥ መገኘት ነው• ስኪዞፍሬኒያ- ይህ ህመም ለብዙ ጊዜ የሚቆይ አደገኛና በህመምተኛው ላይ ከፍተኛ ጫና የሚፈጥር የአዕምሮ ህመም ነው፡፡• የአመጋገብ እክል- ይህ ህመም ሠዎች ከምግብና ከሠውነት ገፅታ/ቅርፅ ጋር ያላቸው ግንኙነት ላይ የተመሠረተ ነው፡፡ ድባቴ ድባቴ፡-በብዛት የሚከሠት የአዕምሮ ህመም ሲሆን በአለም ላይ ከ 264 ሚሊዮን በላይ የሆኑ ሠዎች በዚህ ህመም ይጠቃሉ፡፡ድባቴ ራስን በራስ ወደ ማጥፋት ሊያመራ የሚችል ህመም ሲሆን በዚህም በአለም ላይ በየአመቱ ወደ 800,000 የሚጠጉ ሠዎች ራስን በራስ ያጠፋሉ፡፡ ከመካከለኛ እስከ ከፋ የድባቴ ህመም ላይ ለሚገኙ ህሙማን ውጤታማ የሆነ የስነልቦና እና የመድሀኒት ህክምናዎች ይሰጣሉ፡፡ የመርሳት ህመምየመርሳት ህመም ከአዕምሮ ህመሞች አንዱ ሆኖ ቀስ እያለ በሂደት የሚመጣ የማስታወስ ችሎታን የሚቀንስ የህመም አይነት ነው፡፡ የመርሳት ህመም በብዛት የሚከሰተው በዕድሜ የገፉ ሠዎች ላይ ሲሆን በተቀሩት የዕድሜ ክልል ውስጥ ያሉ ግለሰቦችም ዕድሜ ከገፋት አንፃር ሥርጭቱ ይነስ እንጂ ሊጠቁ ይችላሉ፡፡በአለም ላይ 50 ሚሊዮን ሠዎች የመርሣት ህመም ያለባቸው ሲሆን በየአመቱ 10 ሚሊዮን የሚጠጉ አዳዲስ ተጠቂዎች ይኖራሉ፡፡ የአልዛይመር ህመም ይህ ህመም በዋነኝነት የሚመጣው በአንጎላችን ውስጥ የተለያዩ የማይፈለጉ ፕሮቲኖች ጥርቅም ከመፈጠራቸው የተነሣ በሂደት ጤናማ የአንጎላችን ህዋሳት በሚገባ ሥራቸውን እንዳያከናውኑ ሲያደርጓቸው ነው፡፡ ይህ ህመም ለመርሣት ህመም እንደ ምክንያት ከሚጠቀሱት ውስጥ ከ 60-70% ይሸፍናል፡፡የመርሣት ህመም መነሻ ምክንያቶች- የአልዛይመር ህመም- የኤች አይቪ ኤድስ ህመም- አንጎላችን ተደጋጋሚ አካላዊ ጥቃት ሲደርስበት- ሌሎች የአዕምሮ ህመሞች- ሌሎች አካለዊ ህመም አይነቶች፤የቪታሚን እጥረት፤ የእንቅርት ህመም፤ የደም መርጋት ችግር ወዘተ…- ለረጅም ጊዜ ማጨስና አልኮልን አዘውትሮ መጠጣት የመርሳት ህመም ምልክቶች- የመርሳት ችግር፡- ያስቀመጡትን ዕቃ መርሣት÷ቀጠሮ መርሳት÷ ዕቃ ገዝቶ መልስ መቀበል መርሳት÷የሚያውቁትን ሰው ስም መርሳትና ህመሙ እየተባባሰ ሲሄድ የቤተሰብ ስም ሳይቀር ሊረሱ ይችላሉ፡፡- ግራ መጋባት ፡- ያሉበትን ቦታ በቀላሉ መረዳት ስለሚሳናቸው ከቤት ወጥቶ በዛው መቅረት – ለብዙ አመታት ሲጠቀሙበት የነበሩትን ዕቃ ለመለየት መቸገር – ለመናገር ፈልገው ቃላቶችን ማጣት- በፊት በየቀኑ በቀላሉ የሚያከናውኗቸው ስራዎችን ለማከናወን መቸገርለምሳሌ፡- ጫማ ማሰር÷ቁልፍ መቆለፍ ወዘተ…- ያለምክንያት መዞር- ቁጡ መሆንና በጩኸት መናገር- ተጠራጣሪ መሆን- እንቅልፍ ማጣት ወዘተ ስኪዞፍሬኒያየስኪዞፍሬኒያ ህመም ባህሪያት – ለብዙጊዜ የሚቆይ አደገኛ እና በህመምተኛው ላይ ከፍተኛ ጫና የሚፈጥር የአዕምሮ ህመም ነው፡፡• የስኪዞፍሬኒያ ህመምተኞች በጆሮአቸው ለሌሎች የማይሰማ ድምፅ ለነሱ ይሰማቸዋል፡፡ እነሱ የሚያስቡትን ሰዎች የሚያውቁባቸው ይመስላቸዋል፡፡- ያለምንም ምክንያት ሰዎች ሊጎዱዋቸው እንደተነሱ አድርጎ ማሰብ፡፡ እነዚህ ስሜቶች እና አስተሳሰቦች ህመምተኛውን የሚያስጨንቁና ፍርሀት የሚፈጥሩ ስለሆኑ ከሰዎች መገለልን ያስከትላሉ፡፡- ህመምተኞች ሲያወሩ የሚናገሩትን ለመረዳት አስቸጋሪ ነው- ለብዙ ሰአት አንድ ቦታ ላይ ሳይናገሩም ሆነ ሳይንቀሳቀሱ የመቆምና ስለምን እንደሚያስቡ ሣይታወቅ ደህና መስለው ሊታዩ ይችላሉ፡፡በአጠቃላይ በአለም ላይ 970 ሚሊዮን ሰዎች የአዕምሮ ጤና እክል ወይም በሡስ አስያዥ ንጥረ ነገሮች ተጠቂ ናቸው፡፡- ከአእምሮ ህመሞች መካከል ጭንቀት በአብዛኛው የሚከሰት የአዕምሮ ህመም ሲሆን በአለም ላይ 284 ሚሊዮን ሰዎች የዚህ ሰለባ ናቸው፡፡- በአለም አቀፍ ደረጃ የአዕምሮ ህመም ከወንዶች በበለጠ ሴቶች ተጠቂ ናቸው፡፡ በዚህም ሴቶች 11.9% የመጠቃት እድል ሲኖራቸው ወንዶቹ ደግሞ 9.3% የመያዝ አጋጣሚ አላቸው፡፡ በአጠቃላይ በአለም ላይ ከሚከሠተው የሞት መጠን የአዕምሮ ህመም 14.3% አስተዋፅኦ እንዳለው የሚገመት ሲሆን ይህም በአመት 8 ሚሊዮን የሚጠጋ ሞት እንዳለ ያመላክታል፡፡* የአዕምሮ ህመምና አለም አቀፋዊ ይዘት- በዓለም ላይ 284 ሚሊዮን ሰዎች በጭንቀት ይጠቃሉ፡፡- ድብርት 264 ሚሊዮን የአለምን ህዝብ ለጉዳት ይዳርጋል፡፡- 71 ሚሊዮን የሚሆነው የአለም ህዝብ አልኮልን አብዝቶ በመጠቀም ለጉዳት የሚዳረግ ነው፡፡- የሁለት ተቃራኒ ጫፍ ህመም (ሽቅለት) 46 ሚሊዮን የሚሆነውን የአለማችንን ህዝብ ይጎዳል፡፡- ሲኮዞፍሬኒያ፡- 20 ሚሊዮን የሚሆነውን የአለማችንን ህዝብ ያጠቃል፡፡- በመጨረሻም 16 ሚሊዮን የሚሆን የአለማችን ህችቦች የአመጋገብ እክል (eating disorder) ያለባቸው ናቸው፡፡ ራስን ማጥፋት – በአለም ላይ በየአመቱ ወደ 800,000 የሚጠጉ ሰዎች ራሳቸውን ያጠፋሉ፡፡- ራስን ማጥፋት ከ15-19 የዕድሜ ክልል ውስጥ ለሚገኙ ሰዎች በ3ተኛ ደረጃ ላይ የሚገኝ የሞት ምክንያት ነው፡፡በአለም ላይ 79% ራስን በራስ የማጥፋት ድርጊት የሚከሰተው በዝቅተኛና መካከለኛ ገቢ ባላቸው ሀገሮች ውስጥ ነው፡፡ *ራስን የማጥፋት ሀሳብ እቅድና ሙከራ መንስኤዎችከመቶ ዘጠና አምስት(95%) ያህሉ ራስን የማጥፋት ሃሳብ እቅድና ሙከራ ያለባቸው ግለሰቦች የአዕምሮ ህመም አለባቸው፡፡ ከነዚህም ውስጥ በአብዛኛው መንስኤ ሊሆኑ የሚችሉት – የድብርት ህመም- የአልኮልና ሱስ አስያዥ እፆች ተጠቃሚነት- ሌሎች የአዕምሮ ህመሞች÷ሥነ-ልቦናዊ ጫናዎችና ማህበራዊ ሁኔታዎች *ራስን የማጥፋት ሃሳብ፣ዕቅድና ሙከራ መኖሩን የሚጠቁሙ ምልክቶችአብዛኛውን ጊዜ ራሳቸውን ለማጥፋት ሃሳብ፤ ዕቅድ ያላቸው ሠዎች ይህን ሃሣባቸውን የሚጠቁም ፍንጭ ለቤተሰብ አባላት፣ለጓደኛ፣ለመምህር ወይም ለሃኪም ይሰጣሉ፡፡ ከነዚህም ምልክቶች ውስጥ ጥቂቶቹ፡– ስለሞት ወይም ራስን ስለማጥፋት ደጋግሞ ማንሳት- ድንገተኛ የባህሪ መለወጥ (ለምሳሌ ሁልጊዜ ድብርት ውስጥ የነበረ ሠው በድንገት ደስተኛ መሆን)- ራስን በሚጎዱ ተግባራት የመጠመድ ያልተለመደ ባህሪ- ጤናማ ያልሆነ የቤተሰብ ግንኙነት(መገለል/መጋጨት)- ለአደጋ የሚያጋልጡ ባህሪያት ማሣየት (ከመጠን ባለፈ ሁኔታ የአልኮል መጠጥ መጠጣት፣በአደገኛ ሁኔታ መኪና መንዳት፣ልቅ ወሲብ መጀመር ወዘተ…)- የማያቋርጥ የድብርት ህመም ምልክቶች ለሣምንታት መታየት – ንብረትን ያለአግባብ ማባከን ወይም መስጠት ወዘተ ናቸው፡፡አልኮል በዓለም ለይ በየዓመቱ የ3 ሚሊዬን ሠዎች ሞት የሚከሰተው አልኮል ያለአግባብ ከመጠቀም የሚመጣ ሲሆን ይህም ከአጠቃላይ የሞት ምጣኔ 5.31% ይሸፍናል፡፡ በዓለም ላይ ካሉ የበሽታዎች ጫናና ጉዳት ውስጥ 5.1% የሚሆነው በአልኮል ምክንያት አማካኝነት የሚከሰት ነው ፡፡ከ20-39 ባለው የእድሜ ክልል ውስጥ 13.5% የሚሆነው ሞት በአልኮል አማካኝነት የሚከሰት ነው ፡፡የሚጥል ህመምበዓለም ላይ 50 ሚሊዬን ሠዎች የሚጥል ህመም አለባቸው ከነዚህም ውስጥ 80% የሚሆኑት የሚጥል ህመም ተጠቂዎች ዝቅተኛ እና መካከለኛ ገቢ ባላቸው ሃገራት ውስጥ የሚገኙ ናቸው፡፡3/4ኛ የሚሆኑ የሚጥል ህመም ያለባቸው ሰዎች በዝቅተኛ ገቢ ሃገራት የሚኖሩና በሚፈለገው አግባብ ህክምና የማያገኙ እንደሆነ ጥናቶች ያረጋግጣሉ ፡፡በዓለም ላይ ከሚጥል ህመም ጋር የሚኖሩ ግለሰቦች እንዲሁም ቤተሰቦቻቸው አድሎና መገለል ይደርስባቸዋል፡፡

1 comment so far

A WordPress Commenter Posted on 6:09 am - Dec 27, 2021

Hi, this is a comment.
To get started with moderating, editing, and deleting comments, please visit the Comments screen in the dashboard.
Commenter avatars come from Gravatar.

Comments are closed.

Copyright © 2021 | AMSH| Amanuel Mental Specialized Hospital