Publications

publications

ማህደረ-ጤና
የሚጥል ህመም (ኢፒለፕሲ)
የሚጥል ህመም (ኢፒለፕሲ) ማለት በአንጎል ነርቮች ላይ ተገቢ ባልሆነና በበዛ የኤሌክትሪክ ፍሰት የሚከሰት ሲሆንም ልክቶቹም በተለምዶ የሚታወቀው በሚጥልና ራስን ስቶ በመውደቅ ሲሆን አንዳንድ ጊዜ ራስ ሳያስት እንዲሁም ሳይጥል በአንድ ጎን ማንቀጥቀጥ ብቻ ሊከሰት ይችላል፡፡
የሚጥል በሽታን የሚያመጡ ምክንያቶች
• ከወሊድ በፊትና በወሊድ ጊዜ ህፃኑ ላይ የሚደርስ አደጋ ዋነኛ ምክንያት ነው፡፡ ይህም ብዙ ጊዜ ከእናት ህመምና አስቸጋሪ ምጥ ጋር ሊያያዝ ይችላል፡፡
• በአንጎል ውስጥ በተፈጥሮ ያልተስተካከለ ወይም የጎደለ ክፍል ሲኖር
• በህፃንነት ጊዜ የነበሩ ሃይለኛ የትኩሳት በሽታዎች
• የአንጎል ኢንፌክሽን ለምሳሌ እንደማንጅራት ገትር የአንጎል ወባ ወዘተ
• አንጎል ውስጥ የሚያድጉ እጢዎች
• በሰውነት ውስጥ የሚገኙ ሰውነትን የሚጠቅሙን ንጥረነገሮች በልክና በትክክል አለመገኘት፡፡ ለምሳሌ በደም ውስጥ የስኳር መጠን ማነስ፡፡
• በተለያየ አደጋ ጭንቅላት ሲመታና አንጎል ላይ አደጋ ሲደርስ፡፡
• የአካል በመርዝ መበከል ለምሳሌ ራስን ለማጥፋት ተብለው የሚወሰዱ እንደ ማላታይን የመሳሰሉ መድሃኒቶች
• የአንጎልን ነርቭ የሚጎዱ ህመሞች
• ለብዙ አመታት አልኮል መጠቀም
• በዘር መተላለፍና የመሳሰሉት ናቸው
የሚጥል ህመም አይነቶች
1 ግራንድ ማልሲዠር
ምልክቶች
 ከመውደቃቸው ከተወሰነ ደቂቃ፤ ሰኣት ወይንም ቀን በፊት የሚሰሙ የመረበሽ ስሜቶች
 ከመውደቃቸው ከጥቂት ሴኮንዶች በፊት የሚፈጠር ስሜት ይህስሜት የሚገለፀው ለምሳሌ የፍርሃት ስሜት መሰማት፤ ወዘተ ሊሆን ይችላል
 ሲዠር (ማንቀጥቀጥ) ከዚህ ጋር ተያይዞ የጡንቻ መሳሳብ የሰውነት መገታተር እና መንቀጥቀጥ እንዲሁም ራስን እንደሳቱ መቆየት፤ሽንት መልቀቅ፤ አረፋ መድፈቅ ይከሰታሉ
 ከነቁ በኋላም የመርሳት ፤ ከባድ እንቅልፍ እና የራስ ምታት ስሜቶች ይከሰታሉ
2 ፔቲትማል (አብሰንስ)
• በብዛት የሚፈጠረው በህፃናት ላይ ነው ምልክቶች
1. ምልክቶቹ ከመፈጠራችወ በፊት ምንም ስሜት አይስማቸውመ
2. በድንገት ንቃተ ህሊናቸውን ያጣሉ፣መንቀሳቀስ ያቆማሉ፣መነጋገር ያቆማሉ፣ወደ አንድ አቅጣጫ አይናቸው ይቀየራል
3. የአይን ሽፋሽፍት፣የፊት ጡንቻ እና የጣት መንቀጥቀጥ ይታይባቸዋል
4. አንዳንድ ጊዜ ከንፈር መምጠጥ እና ማኘክ ይታይባቸዋል
 እነዚህ ከላይ የተጠቀሱት ምልክቶች የሚቆዩት በአብዛኛው ለ10 ሰከንድ ያህል ሲሆን በተደጋጋሚ ሊከሰት ይችላል
በተወሰነ የሰውነት ክፍል ላይ ብቻ የሚከሰት ኢፒለፕሲ ዓይነቶች (ሲምፕል ፓርሻል ሲዠር)
2.1 ሲምፕል ፓርሻል ሲዠር
የፓርሻል ሲዠር አይነት ሲሆን ምልክቱም
1.በአንድ አቅጣጫ አንገት እና አይንን መጠምዘዝ
2.በአንድ ጎን እጅና እግርን ማንቀጥቀጥ ሊሆን ሲችል፡ ነገር ግን እራስን መሳትም ሆነ መሬት ላይ መውደቅ አይከሰትም
2.2 ኮምፕሌክስ ፓርሻል ሲዠር
ሌላኛው የፓርሻል ሲዠር ዓይነት ሲሆን ምልክቶቹም
 ህመሙ ሲጀምር የተለያዩ ስሜቶች ሊከሰቱ ይችላሉ ለምሳሌ ከተፈጥሮ ውጪ የሆነ (የሌላ) ድምጽ መስማት፣ ማየት እና የእይታ መጭበርበር፡፡
 አካባቢን በአግባቡ የመረዳትና የመገንዘብ ችግር
 የተለያዩ በባህሪ ለውጥ የሚገለጹ ምልክቶች ለምሳሌ ከንፈር መምጠጥ፣መሳቅ፣ መሮጥ፣ ራቆት መሆን፣ መቆጣትና ስሜታዊነት
 ከላይ ከተጠቀሱት ምልክቶች በኃላ የሚከሰቱት በአብዛኛው መርሳት፣ ከባድ እንቅልፍ እና ራስ ምታት የመሳሰሉት ናቸው፡፡
3.ስታተስ ኢፒለፕቲክስ
 በተደጋጋሚ የሚከሰት የሚጥል በሽታ/የኢፒለፕሲ ምልክት ነው
 ብዙ ጊዜ የሚከሰተው መድሃኒት በድንገት በማቋረጥ ወይም በመመረዝ ምክንያት ነው
 ፈጥኖ ሃኪም ቤት ካልተወሰደና ተገቢውን አስቸኳይ የመድሃኒትና ሌላም እርዳታ ካልተደረገለት ሞትን ሊያስከትል ይችላል፡፡
4. ፌብራይል (ከትኩሳት ጋር የተያያዘ)
 የሚከሰተው ህፃናት ላይ ነው፡፡
 ይህንን ህመም የሚያስከትሉ የትኩሳት በሽታዎች እንደ ጉንፋን፣ የጆሮ ኢንፌክሽን የመሳሰሉት ናቸው፡፡
 በዚህ ወቅት በቀዝቀዛ ፎጣ ትኩሳትን ማብረድ እና ህፃኑን ለምርመራ መውሰድ ተገቢ ነው፡፡
ህመምተኛው ማድረግ ያለበት ጥንቃቄ
 የአካልና የአእምሮ ጤንነትን መጠበቅ
 በቂ እንቅልፍ መተኛት
 ሱስ አስያዥ ንጥረ ነገሮችን አለመጠቀም
 ጭንቀትን ማራቅ
 መጠነኛ የሆነ ስፖርትን አዘውትሮ መስራት
 የሚያባብሱ ነገሮችን ማራቅ ለምሳሌ ብርሀን የበዛበት ነገር እንደ ቴሌቭዥን የመሳሰሉት ነገሮች ላይ ረዥም ቆይታ አለማድረግ ናቸው፡፡
በግራንድማል ሲዠር (ሰዎች እራሳቸውን ስተው በወደቁ ሰዓት የሚደረጉ ጥንቃቄዎች)
 ህመምተኛውን ከውሃ አካባቢ፣ ከእሳት አካባቢ እና ከመኪና መንገድ ማራቅ
 ሊጎዱ የሚችሎ ነገሮችን ከህመምተኛው አካባቢ ማራቅ
 ልብሶቹን ማላላት፣ መነጽር ማውለቅ
 ከጭንቅላት ስር ለስላሳ ነገር ማድረግ
 ህመምተኛውን በአንድ ጎን ማስተኛት
 ህመምተኛው እስኪነቃ ድረስ ከህመምተኛው ጋር መቆየት
በግራንድማል ሲዠር (እራሳቸውን በሳቱበት ሰዓት የማይደረጉ ነገሮች)
 በአፍ ውስጥ ምንም አይነት ነገር አለመክተት
 ክብሪት ጭሮ አለማሽተት
 የሚጠጣ ነገር አለማጠጣት
 ማንቀጥቀጡን ለማስቆም አለመሞከር
ለሚጥል ህመም (ኢፒለፕሲ) የሚሰጡ የህክምና አገልግሎቶች
የሚጥል በሽታ ህክምና ከጥቂት ዓመታት እስከ እድሜ ልክ ክትትል ሊያስፈልገው የሚችል የህመም አይነት ነው፡፡ የቅርብ ክትትልና ቁጥጥርም ያስፈልገዋል፡ አንድ ጊዜ ህክምና ከተጀመረ ሃኪሙ መድሃኒቱን መውሰድ አቁም እስከሚል ድረስ ታማሚው መድሃኒቱን በታዘዘለት መጠን እና ሰዓት መውሰድ አለበት፡፡ መድሃኒቱን በድንገት ማቋረጥ ሀይለኛ የሚጥል በሽታ እንዲያገረሽ ያደርጋል፤ በሽታው መጣሉን ቢተውም እንኳን መድሃኒቱን ማቋረጥ አይገባም፡፡
ሊደረጉ የሚገቡ ጥንቃቄዎች
 መድሃኒቱን ህፃናት በማይደርሱበት ቦታ ማስቀመጥ
 ሩቅ መንገድ ከሄዱ መድሃኒቱን ይዞ መሄድ
 መድሃኒቱን ሙሉ በሙሉ ከመጨረሱ በፊት ሌላ ተጨማሪ ማሳዘዝ
የሚጥል ህመም የማይተላለፍባቸው መንገዶች
 በንክኪ
 በምራቅ
 በህመሙ ምክንያት የወደቀውን ሰው በመርዳት አይተላለፍም
የሚጥል በሽታ እርግማን አይደለም! ህክምናም አለው!
 በህክምና ሙሉ ለሙሉ ወይም በከፊል መቆጣጠር ይቻላል
 የሚጥል በሽታ መድሃኒት በየቀኑ ሳይቋረጥ ረዘም ላለ ጊዜ መወሰድ አለበት፡፡

ስለማሰብ ማሰብ

አንድ ተማሪ ፈተና ላይ ‘የሱዳን ዋና ከተማ ማን ነው?’ ለሚለው ጥያቄ ‘ናይሮቢ’ ብሎ መልሶ ከወጣ በኃላ ይጠራጠርና ‘ፈጣሪዬ የሱዳንን ዋና ከተማ ኖይሮቢ አድርገው’ ብሎ ፀለየ። የተናገርነው ነገር ወይም ያደረግነው ድርጊት ትክክልም ስህተትም ሊሆን እንደሚችል መጠርጠር ጥሩ ነው። አለበለዚያ ከአፈርኩ አይመልሰኝ ስህተት ላይ ስህተት መደራረብ በመጨረሻም ጭንቀት ይፈጥራል።

የሰው ልጆች እጅግ አስደናቂ ችሎታችን ማሰብ ከመቻላችን በላይ ስለማሰብ ማሰብ መቻላችን ነው፡፡ ስለማሰብ ማሰብ የምናስብበትን መንገድ ለማሻሻል ከማስቻሉም በላይ ሌሎች ሰዎችን በተሻለ ለመረዳት ያስችላል፡፡ ስለምናስበበት መንገድ አብዝተን ባሰብንና ስለሀሳቦቻችን የተረዳነውን ተግባር ላይ ስናውል የበለጠ ደስተኛ የበለጠ ውጤታማ እንሆናለን፡፡

ሀሳባችን እውነታውን ሊወክልም ላይወክልም ይችላል፡፡ “እኔ ያሰብኩት ብቻ ነው እውነታው!” ብሎ ክችች ማለት ስለማሰብ እያሰብን እንዳልሆነ ያሳያል፡፡ በእንግሊዘኛው Psychic equivalence ይባላል፡፡ምናባችንን ወደ እውነታው ከማምጣት እውነታውን ወደ ምናባችን ለማምጣት እንደመጎተት ነው፡፡

ሀሳባችን ማለት ሙሉ ለሙሉ እኛን አይወክልም፡፡ ሀሳባችን የኛ እንጂ እኛ አይደለም፡፡ ይህን ስንረዳ ሌሎች ከኛ የተለየ፣ ተቃራኒ ወይም የትችት አስተያየት ሲሰነዝሩ “ተጠቃሁ!!” ብሎ ለአፀፋ ከመዘጋጀት ይልቅ “እኔም አንዳንዴ የማስበው ሀሳብ ልክ እንዳልሆነ ይገባኛል፡፡” በማለት ሚዛናዊ እንድንሆን ያስችለናል፡፡

ስለማሰብ ማሰብ የአስተሳሰብ ስህተቶቻችንን መለየት፣ ጠቃሚ የሆኑትን ማጠናከር እና ሂደቱን በተከታታይ ማስተዋል ነው፡፡ የንግግር ህክምና(Psychotherapy) በቀላሉ ሲገለፅ ሰዎች ከሀሳባቸው ትንሽ ወደ ወደ ኃላ ብለው ሀሳባቸውን በራሳቸው መመርመርና መለወጥ እንዲችሉ ማገዝ ነው እንጂ ብዙዎች እንደሚመስላቸው ሰዎችን መምከር አይደለም፡፡

አስተሳሰባችንን ስንለውጥ አለማችንን ቢያንስ በትንሹ መለወጥ እንችላለን፡፡

መልካም ጊዜ!
ዶ/ር ዮናስ ላቀው

ትኩረት የሚሹ የህፃናትና ወጣቶች የአዕምሮ ጤና ችግሮች

ትኩረት የሚሹ የህፃናትና ወጣቶች የአዕምሮ ጤና ችግሮች
I. በህፃናት ላይ የሚታዩ የባህሪና የአዕምሮ ችግሮች
1 የሱሰኝነት ችግር
ሱስ የሚያሲዙ ነገሮች የሚባሉት መጠጥ፤ ጫት፤ ሲጋራ፤ ሃሺሽ የመሳሰሉት ናቸው፡፡
በህብረተሰቡ ውስጥ ስሜትን ለማነቃቃትና ለማስተካከል ሲባል የተለያዩ ነገሮችን መጠቀም የተለመደ ነገር ነው፡፡ አብዛኛው ሰው ቡና፤ ሻይ ወይንም የተለያዩ መጠጦችን ይወስዳል፡፡
ልጆችም በጉርምስና የእድሜ ክልል በሚደርሱበት ጊዜ ከቤተሰብ ቁጥጥር ውጭ የመሆንና የጀብደኝነት ስሜት ስለሚሰማቸው የተለያዩ ነገሮች ውስጥ ራሳቸውን ሊያገቡ ይችላሉ፡፡ ከእንዚህም አንዱ ሱስ የሚያሲዙ ነገሮችን መጠቀም ነው፡፡
በሱስ ለመጠመድ የሚገፋፉ ዋና ዋና ምክንያች
 ድብርት ወይም ጭንቀት
 ለተለያዩ ጉዳቶችና በደሎች መጋለጥ፤ መገለል
 ድህነት፤ ስራማጣት፤ ተስፋ መቁረጥ
 ሱሰኛ ከሆኑ ወላጆች ወይም አሳዳጊዎች ጋር መኖር
 ከጓደኞቻቸው ተመሳሳይ ሆኖ ለመታየት
ይህ ሁኔታ በአሁኑ ወቅት በአለም ደረጃ በህብረተሰቡ ጤንነት ላይ ችግር ፈጣሪ መሆኑ ተደርሶበታል፡፡ የስልጣኔ መስፋፋት ደግሞ ለህገ ወጥ ሱስ አስያዥ መድሃኒቶች በቀላሉ መገኘት ትልቅ አስተዋፅኦ አለው፡፡ ማለትም ቴክኖሎጅው ባደገ ቁጥር አዳዲስ ሱስ አምጭ ነገሮች እየተፈበረኩ ነው፡፡ የትራንስፖርት ዘዴዎች ደግሞ ለእነዚህ ነገሮች መሰራጨት ሰፊ ሚና እየተጫወቱ ነው፡፡ በመሆኑም ለችግሩ መስፋፋት ስልጣኔ የራሱ አስተዋፅኦ አለው፡፡ በአለም ላይ የጎላ ችግር የማስከተሉን ያህል የስርጭቱ ሁኔታ ብዙም አይታወቅም፡፡
በሱስ መጠመድ ምክንያት ከሚከሰቱ ችግሮች ጥቂቶቹ የሚከተሉት ናቸው፡፡
 ለአደጋ መጋለጥ
 ራስን ማጥፋት
 ሽብርተኝነት
 ያልተፈለገ ዕርግዝና
 የአባላዘር በሽታዎች ኤች ኤይ ቪ ጭምር እና ወዘተ ናቸው፡፡
ህክምናና ቅድመ ጥንቃቄዎች
አንድ ልጅ ባህሪው ሲለወጥ፤ በህብረተሰቡ ውስጥ ያለውን እንቅስቃሴ ጤናማ ሳይሆን ሲቀር ወይም በትምህርት ሲደክም ወላጆችና መምህራን ወይም ጓደኞቹ በሱስ ተጠምዶ ሊሆን ይችላል ብልው መጠራጠር ይኖርባቸዋል፡፡ በሱስ የተጠመደ ልጅ የህክምና አገልግሎት ማግኘት አለብህ፡፡
ለሱስ የሚሰጠው የህክምና ዓይነት እንደሚጠቀመው የዕጽ ዓይነትና የቆይታ ጊዜ የተለያየ ነው፡፡ በህክምናም ልጁ የሚጠቀመውን ነገር በአንድ ጊዜ እንዲያቆም ማድረግ ወይም በቡድን ማለትም ከሌሎች በሱስ የተጠመዱ ሰዎች ጋር ሆኖ ደረጃ በደረጃ እንዲያቆም ማድረግ ይቻላል፡፡ አስፈላጊ ከሆነም በሆስፒታል ሆኖ ህክምና ይደረግለታል፡፡ ለህክምናው መሳካት የበሽተኛውና የቤተሰብ ፈቃደኝነትና ትብብር አስፈላጊ ነው፡፡
በልጅነት ወቅት የሚከሰቱ አስቸጋሪ ባህሪያት
እነዚህ የባህሪያት ችግሮች የሚታወቁት በተደጋጋሚ በሚታዩ ለህብረተሰብ ጠንቅ የሆኑ ባህሪያት ሲታዩና እነዚህም በልጆች የት/ቤት፣ የቤትና የአካባቢ የኑሮ ሁኔታዎች የጎላ ችግር ሲፈጠርባቸው ነው፡፡ እነዚህ ችግሮች በህጻንነትና በጉርምስና የእድሜ ክልል በሚገኙ ልጆች የአዕምሮ ጤንነት ላይ ችግር ከሚፈጥሩ ህመሞች ውስጥ ዋናዎቹ ሲሆን በዓለም ከሚገኙ ወጣቶች 6 ከመቶውን ያህል ያጠቃልላል፡፡
ሕመሙ አለ የምንለው መቼ ነው
ይህ የባህሪ ችግር ከእምቢተኝነትና ተቃራኒነት አንስቶ እስከ የጎላ የባህሪይ ብልሹነትያሉትን ችግች ያጠቃልላል፡፡
ሀ/ የእምቢተኝነትና ተቃራኒነት ባህሪይ ምልክቶች
 ግልፍተኝነትና አኩራፊነት
 ከአዋቂ ጋር በተደጋጋሚ አላስፈላጊ ጭቅጭቅ ውስጥ መግባት
 እምቢተኝነት
 ሆን ብሎ ሰዎችን በነገር ማበሳጨት
 በራሳቸው ጥፋት ሌሎች ሰዎችን መውቀስ
 ማስቆጣት
 ብስጩነት፣እልኸኝነት/ቂም በቀለኝነት
ለ/ ከዚህ የጎላ የባህሪይ ችግር ደግሞ ብልሹ ባህሪይ(Conduct Disorder) ተብሎ የሚታወቅ ሲሆን በሚከተሉት ምልክቶች ይገለጻል
 ውሸታምነት፣ ማጭበርበር፣ ማታለል
 ጠብ ጫሪነት፣ ተደብዳቢነት
 እንሰሳትን መደብደብ
 ሌሎችን ሆን ብሎ መጉዳት
 ለጥፋት ተነሳሽነት
 ሌብነት
 አስገድዶ መድፈር፣ ለአካላ መጠን ሳይደሰርሁ ወሲብ መፈጸም፣ ሴሰኝነት፣
 ወንጀለኝነት
ለዚህ ባህሪይ መፈጠር አስተዋጽኦ የሚያደርጉ ነገሮች
1/ በቤተሰብ አካባቢ
ብጥብጥ የበዛበት ቤተሰብ
የእንክብካቤ ማነስና የተለያዩ በደሎች
ጠጪነትና ሌሎች እፆችን ተጠቃሚነት
የወላጆች አዕምሮ ህመም
በኤች አይ ቪ ኤድስ በመያዝ ወይም ሌሎች ምክንያቶች ተገቢውን እንክብካቤ አለማግኘት
2/ ድህነት/የባህል ተፅዕኖዎች
• ለኑሮ አስፈላጊ የሆኑ መሰረታዊ ፍላጎቶች አለመሟላት
3/ በአስተዳደግ ወቅት በጥሩ ስነ-ምግባር አለመቀረፅ
4/ በተለያዩ የአዕምሮ በሽታዎች በጋራ መኖር ለምሳሌ የመቅበዝበዝና የማስተዋል ችግር
መፍትሄዎች
ልጆች የተወሰነ የእድሜ ክልል በሚደርሱበት ጊዜ የእምቢተኝነት ባህሪ ሊከሰት ይችላል፡፡ ነገርግን በኑሮአቸውና ስራቸው ላይ ችግር ሲፈጥር ለህመሙ መፍትሄ መፈለግ ይኖርበታል፡፡
የባህሪ ለውጥ ለማምጣት ብዙ ጥረት ይደረጋል፡፡ በአጠቃላይ የምክር አገልግሎት ማለትም ጥሩ ስራዎችን ማበረታታትና መጥፎ ስራዎችን ንቆ መተው ወይም በአግባቡ መቃወምን ያጠቃለለ ሲሆን ስራውም የሚሰራው በአብዛኛው በወላጆችና ት/ቤት አካባቢ ነው፡፡
ይህ ብዙ ለውጥ የማያመጣ ከሆነ ወደ ሃኪም ተወስደው እንደ ምልክቶቹ ሁኔታና የቆይታ ጊዜ የተለያዩ የባህሪ ለውጥ የሚያመጡ መድሃኒቶችን መጠቀም ይቻላል፡፡
ሐ. ድብርት
ወላጆች ወይም አሳዳጊዎች ምን ማወቅ አለብን
ድብርት ማለት አለመደሰት ወይም ማዘን ብቻ ሳይሆን ከበድ ያለ የአእምሮ ችግር ነው፡፡
ድብርት ያለባቸው ልጆች ከሚከተሉት አብዛኛዎች ሊኖራቸው ይችላሉ፡፡
እነዚህም
 ሐዘን፤ቁጣ፤ተስፋ መቁረጥ፤ፀፀት
 ራስን ማግለልና ብቸኛ መሆን፤ ደስታ ማጣት
 በፊት የሚወዱትንና የሚያስደስታቸውን ሁሉ እርግፍ አድርጎ መተው
 ሐሳብን ማሰባሰብ አለመቻል፤ መርሳት፤ በዚህም የተነሳ በትምህርት ድክመት ማሳየት
 በራሳቸው የነበረው እምነትና ጥንካሬ መጥፋት
 የምግብ ፍላጎት መቀነስና ክብደት መቀነስ ወይም በተቃራኒው በጣም መብላትና መወፈር
 የእንቅልፍ መዛባት ይህም ሲባል በማለዳ ሳይፈልጉ መንቃት ለመተኛት ቢፈልጉም እንቅልፍ አለመውሰድ፤ ወይም ብዙ ጊዜ መንቃት
 ያለ ምክንያት ድብርት በተወሰነ ሰዓት መምጣትና ያም ሰዓት እያለፈ ሲሄድ የተሻለ መሆን ለምሳሌ ጠዋት መደበትና እየመሸ ሲሄድ ደህና መሆን
 መጥፎ ሃሳቦች ለአዕምሮ መመላለስና እነዚህንም ልጆች በቃል ሲናገሩ ሊደመጡ ይችላሉ፡፡ ለምሳሌ ራስን ለመጉዳት ወይም ለማጥፋት፣ ሌሎችን ለመጉዳት ማሰብ የመሳሰሉት
 አንዳንድ ጊዜም ልጆች መጠጥ ሲጠጡና ሌሎች ሱስ የሚያሲዙ ነገሮችን ሲጠቀሙ ምክንያቱ ድብርት ሊሆን ስለሚችል ባለሙያ ማማከር ይጠቅማል፡፡
በአጠቃላይ ድብርት ያለባቸው ልጆች ግራ መጋባት በመኖር ትርጉም ማጣትና አለመደሰት፤ መፀፀጽ፤ በአእምሮም ሆነ በአካል መድከም ስለሚያጠቃቸው ከዚህ ሁሉ ለመገላገል ራስ ማጥፋት እንደመፍትሄ ሊጠቀሙበት ይችላሉ፡፡ ሲጠቀሙበትም ይስተዋላል፡፡
ድብርት ምን ያህል ይቆያል
ጤናማ ጭንቀት ወይም ሃዘን ምክንያታዊና ገደብ ያለው በመሆኑ ብዙ የሚቆይ አይደለም፡፡ በዚህም የተነሳ ይህ ችግር በልጆች ላይ ከሁለት ሳምንት በላይ ከቆየ ችግሩን በፅሞና መከታተል ያስፈልጋል፡፡ ይህም ሆኖ ድብርቱ ከቀጠለና በተለይም ከ3 ወር ካለፈ አጣዳፊ የህክምና ወይም የምክር አገልግሎት ወደምናገኝበት ቦታ መሄድ ተገቢ ነው፡፡
ወላጆች ምን ማድረግ እንችላለን
ድብርት ለተወሰነ ጊዜ የሚቆይና በሃኪም እርዳታ ሊድን የሚችል ነው፡፡ ልጆች ይህ ችግር ሲያጋጥማቸው ችግራቸውን መረዳትና ብዙ ጊዜ ከእነሱ ጋር በመሆን ከጎናቸው መሆናችንን እንዲያውቁ ማድረግ ጠቃሚ ነው፡፡
መ. ጭንቀት/Anxiety/ ምን ማለት ነው
ጭንቀት ማለት ፍርሃት ከልክ በላይ ሲሆንና ለረጅም ጊዜ ከግለሰቡ ጋር ቆይቴ በግለሰቡ ህይወት ወይም የዕለት ከዕለት ክንውን ላይ አሉታዊ ጫና ሲፈጥር የምናየውን ችግር የምንገልፅበት ነው፡፡
እንደ ወላጅ ማወቅ ያለብን የልጆችን ፍርሃት ወይም ጭንቀት ከአጋጠማቸው ሁኔታ ጋር ሲነፃፀ ር ተመጣጣኝ ነው ወይንስ አይደለም የሚለውን ነው፡፡
ለምሳሌ ድመትን አይቶ ነብር ያየ ያክል መፍራት ፍርሃቱ መጠኑን ያለፈ እንደሆነ ያስረዳናል፡፡
የልጆችን የጭንቀት መጠን ለማወቅ የሚከተሉትን 3 ነጥቦች ማጤን ያስፈልጋል
1 የኔ ልጅ ጭንቀት ሌሎች እንዳለባቸው አይነት ነውን
ለምሳሌ ከሶስት አመት በታች ያሉ ህፃናት ከወላጅ በሚለዩበት ጊዜ የሚያሳዩት አይነት መረበሽ ወይም ደግሞ ልጆች በትምህርት መጀመሪያ እድሜጣቸው አካባቢ ትንንሽ ነፍሳትን፤ አዲስ ሰውን ወይም አጋጣሚን ሲያ የሚያሳዩትን አይነት ፍርሐት
2 የኔ ልጅ ጭንቀቱን መግለፅ ማስረዳት ይችላልን
ልጆች በብዛጽ ጭንቀጻቻን መግለፅ አይችሉም ይህንንም በመረዳት ወላጆች የልጆቻቸው ባህሪ ሲለወጥ ስሜታቸውን ፈጥኖ የመረዳት ሓላፊነት አለባቸው፡፡ ይህን ለማድረግ በአጭሩ በቂ ሰዓት መተኛታቸውን፤ ት/ቤት በብዛት አለመቅረታቸውን ከሌላው ጊዜ በተለየ መጨነቅ አለማብዛታቸውን ወዘተ…. መከታተሉ በአብዛኛው በቂ ነው፡፡
3 ጭንቀታቸው ምን ያህል ጊዜ ይቆያል
መጠኑንያላለፈ አጭ ጊዜ የሚቆይ ፍርሃት ወይም መጨነቅ የጤናማ ሰው ባህሪ ቢሆንም ይህ ችግር ለሳምንታ ከቆየ በፅሞና መከታተል እንዲሁም ደግሞ ከ3 ወር በላይ ከሆነ የባለሙያ እርዳታ መፈለግ አማራጭ የሌለው ይሆናል፡፡
ልጆች ጤናማ ያልሆነ ጭንቀት ሲያጋጥማቸው የሚታዩ ምልክቶች
 ትንፋሻቸው ቁርጥ ቁርጥ ማለትና መፍጠን፤ ማላብ፤ ማቅለሽለሽ፤ ራስ ምታት፤ ማስቀመጥ በአጠቃላይ ጥሩ ስሜት አለመሰማት
 ብዙ ጊዜ ቁጡ መሆን
 ጭንቀት ያመጣብናል ብለው ያሰቡትን ነገር ማስወገድ ከብዙዎች ጥቂቶቹ ናቸው
ልጆች ጭንቀት አለባቸው ካልን እንዴት ልንረዳቸው እንችላለን
መልስ ለመስጠት ሳይቸኩሉ የልጆችን ችግር በፅሞና ማዳመጥና የሚያስጨንቃቸው ጉዳይ ምንም ማለት እንዳልሆነ ለማስረዳት መሞከር የመጀመሪያው ይሆናል፡፡ ከዚህም በተጨማሪ የሚፈሩትን ነገር በዝግታ አደፋፍሮ ለማቀራረብ መሞከር ፡፡ ይህ ሁሉ ሆኖ ግን ለውጥ ከሌለ የባለሙያ እርዳታ ያስፈልጋል፡፡
ሠ/ የትኩረት ማነስ የመቅበጥበጥ ችግር /Attention Deficit Hyperactivity Disorder/
መቅበጥበጥና ትኩረት ማነስ በልጆችላይ በብዛት የሚጣይ የአእምሮ ችግር ነው፡፡
በዚህ ችግር የሚጠቁ ልጆች ከሚታዩባቸው ባህሪያት በጥቂቱ የሚከተሉት ናቸው
አንድ ቦታ ሃሳብን አሰባስቦ መቆየት አለመቻል ተግባራቸው ከሃሳባቸው መቅደም በት/ቤት የሚሰጣቸውን ስራ ማከናወን አለመቻል በአጭሩ ይቅበጠበጣሉ እረፍት የላቸውም ሃይለኞች ናቸው በአንድ ሃሳብ አይረጉም፡፡
ምልክቶቹ ምንምን ናቸው
በአንድ ጨዋታ ወይም ስራ ላይ ረግተው አይቆዩም
የሚነገራቸውን አይሰሙም ወይም አያዳምጡም
የተቀናጀ ስራ መስራት አይችሉም
ጠቀም ያለ ጊዜ ወስደው የአንጎል ስራ መስራት አይውዱም፡፡ ለምሳሌ የቤት ስራ
ለስራቸው ለመጫወቻ የሚያስፈልጓቸውን ነገሮች ይረሳሉ ያጠፋሉ ደብተር እስኪርቢቶ አሻንጉሊት
በቀላሉ ሃሳባቸው ወደሌላ ነገር ይዞራል
አንድ ቦታ መቀመጥ አይችሉም ይቅበጠበጣሉ ለምሳሌ ክፍል ውስጥ መቀመጫ በብዛት ይቀያይራሉ
በፀጥታ መጫወት ወይም መስራት አይችሉም
በጣም ወራሉ
የተጠየቁት ጥያቄ ሳያልቅ መልስ መስጠት ይጀምራሉ
ተራቸውን ጠብቀው መናገር ወይም መጫወት አይችሉም
ህክምናው ችግሩን አጢኖ መረዳትና የባለሙያ እርዳታ ማግኘት ወደ ጎን መባል የሌለበት ጉዳይ ነው፡፡

II. ትኩረት የሚሹ የወጣቶች የባህሪ እና አዕምሮ ጤና ችግሮች

ጥናቶች እንደሚያመላክቱት ከዛሬ አስርት አመታት በፊት በአለም ላይ ካሉት ህፃናትና ወጣቶች ውስጥ እስከ 20 በመቶ የሚሆኑ ልዩ ልዩ የባህሪ ችግሮች ያላቸው ሲሆኑ ከዚህ ውስጥ ከ3-4 በመቶ የሚሆኑ ህክምና የሚያስፈልጋቸው ናቸው፡፡
በህፃናትና ወጣቶች ላይ ከ10 መሪ የጤና ቀውስ ከሚያስከትሉት ምክንያቶች 5ቱ የባህሪይ እና የአእምሮ ጤና ችግሮች መሆናቸውን ጥናቶች ያረጋግጣሉ፡፡
የህጻናትና ወጣቶች አእምሮ በተለያዩ ሰው ሰራሽና ተፈጥሯዊ ችግሮች ሊናጋ ይችላል፡፡ ከዚህም ውስጥ ዋናዋናዎቹ ጦርነት፤ ርሃብ፤ ድህነት፤ የእናቶች አካላዊ፤ ስነልቦናዊና ኢኮኖሚያዊ ችግር፤ የህፃናት ሰብአዊ መብቶች የአለመረጋገጥ ወዘተ በህፃናት ብሎም በወጣቶች ስነ-ልቦናና አእምሮ ላይ ከፍተኛ አሉታዊ ተፅእኖ ያሳድራሉ፡፡
እድገቱን ያልጨረሰው የወጣቶች አእምሮ በተለያዩ ምክንያቶች ባጭሩ ሊቀጭ ይችላል፡፡ ለምሳሌ ራስን ማጥፋት በ3ኛ ደረጃ ላይ የሚገኝ የወጣቶች ሞት መንስኤ ነው፡፡ ሌላው ወጣቶችን ለከፋ የአእምሮ ችግር ከሚያጋልጡት አንዱ ለአደገኛ መድሃኒቶችና ሱስ አምጭ እፆች አለአግባብ አጠቃቀም መሆኑን እንዲሁ ጥናቶች ያትታሉ፡፡ከጦርነት፤ ከመፈናቀል ወዘተ የሚመጡት ከፍተኛ የስነልቦና ቀውሶችና የአእምሮ ህመሞች ወጣቶችለበሽታ መዳረግ ብቻ ሳይሆን ህብረተሰቡንም ወደከፋ የማህበረሰብ ቀውስ ሊከትቱት ይችላሉ፡፡ በተለይም ከላይ የተጠቀሱት ዋና ዋና ምክንያቶች ለዘመኑ አስከፊ የጤናና ማህበራዊ ቀውስ ምክንያት ለሆነው ኤች አይቪ ኤድስ አቀጣጣይ ነዳጅ ናቸው፡፡
ከዚህ በታች የተዘረዘሩት የተለየ ትኩረት ሊሰጣቸው የሚገባ ወዋና ወዋና የወጣቶች የባህሪና ጤና ችግሮች መሆናቸውን ፕ/ር መስፍን አርአያ በ1996 ዓ.ም የስነ አእምሮ ጤና ቀንን ምክንያት በማድረግ በአቀረቡት አውደ ጥናት ላይ አመላክተዋል፡፡
1 ከፍተኛ ጭንቀት(Anxiety disorder)
2 ድብርት (Depressive disorder)
3 የብህሪ ቀውስ (Disruptive behavior disorder)
4 የመማር ቀውስ (Learning Disability)
5 የሱስ አምጭ ንጥረ ነገሮች አለአግባብ ተጠቃሚነት (Substance Abuse)
6 በወጣት ላይ የሚከሰት ራስ ማጥፋት (Teen Suicide)

የወጣቶች የአእምሮ ጤና ከወላጆች የአካል፤ የአእምሮና ማህበራዊ ደህንነት መረጋጋት ጋር በእጅጉ እንዲሚያያዝም በአውደ ጥናቱ ተመላክቷል፡፡ ሁለቱም ወላጆች እርስበርስ በመፋቀር በመከባበርና አርአያነት በአለው አኳኋን በመተሳሰብ በሚኖሩበት እቅፍ ውስጥ የሚያድግ ልጅ ይህ በአንድ ወይም በሌላ ምክንያት ባልተሟላበት ከሚያድግ ልጅ የተሻለ የአእምሮ እርጋታ እድገት እንደሚያሳይ ፕ/ር መስፍን በአቀረቡት ጥናት ላይ አመላክተዋል፡፡
1 ከፍተኛ ጭንቀት
ህፃናትና ወጣቶችን ከሚያጠቁ የአእምሮ ችግሮች አንዱ ከፍተኛ ጭንቀት ነው፡፡ በዚህ ችግር የሚሰቃዩ ወጣቶች ከፍተኛ ምክንያት አልባ ፍርሃት፤የልብ ምት መዛባት፤መበርገግ፤አእምሮን ማሰባሰብ አለመቻል በዚህም ምክንያት ትምህርትን በተገቢው ለመከታተል አለመቻል፤ መነጫነጭ፤ በተደጋጋሚና በቀጣይነት ለረጅም ጊዜ ሊታይባቸው እንደሚችል በጥናቱ ተዳሷል፡፡
2 ድብርት
ይህ የአእምሮ ጤና ችግር ብዙ ጊዜ በተለይ በህፃናት ላይ ሲከሰት አሳዳጊዎች ወይም መምህራን በቀላሉ ሳይገነዘቡት ለከፋ ሁኔታ የሚዳርግ ነው፡፡ ይህም የሚሆነው የህፃናቱ ወይም የወጣቶቹ ባህሪ ዝምተኛ ሲሆን ተቀባይነት ያለው ሆኖ ስለሚገኝ ነው፡፡ በአውደ ጥናቱ እንደቀረበው በተለይ አንድ ወጣት ቀድሞ ከነበረው ባህሪ እጅግ በተለየ ሁኔታ የእንቅልፍ፤ የመሳቅ፤ የመጫዎት፤ ወዘተ ባልተለመደ ሁኔታ ቀንሰው ከሆነ ለድብርት ተጋልጦ ስለሚሆን በሚገባ ቀረብ ብሎ ማስተዋል ተገቢ እንደሆነ ያሳያል፡፡
ድብርት ሃዘንተኛ መሆንን፤ቁጡና ነጭናጫነትን፤ ተስፋ መቁረጥን፤ የበደለኛነት ስሜትን፤ ስለራስ ያለ ግምት ዝቅተኛነትን፤ በወጣቱ ላይ ስከትላል፡፡ ይህ ስሜት እየጨመረ እና እየበረታ ሲሄድ ወጣቱ ከችግሩ ለመላቀቅ ወደ ሱስ አምጭ ንጥረ ነገሮች አለበለዚያም ራስን ለማጥፋ እስከ ማሰብ እንዲደርሱ ያደርጋቸዋል፡፡
3 የባህሪይ ቀውስ
ይህ ችግር በህፃናትና በወጣቶች ላይ የሚታይ ፀረማህበረሰብ የሆነ አቋምና ድርጊት የሚንፀባረቅበት ሁኔታ እንደሆነም ነው ጥናቱ የሚያሳየው፡፡ በዚህም ምክንያት ወጣቱ ትምህርቱን ለመከታተልም ሆነ የመሰል ወጣቶች እንዲሁም የህብረተሰቡን ህግጋትና ባህል በሚገባ ለመከተልማቃት ብቻ ሳይሆን አፍራሽ ድርጊቶች የሚፈፀምበት ነው፡፡ተቃርኖን የሚያጎላ ባህሪ ከማሳየት እስከ ጉልህ የጠባይ ቀውስ ለከሰቱ ይችላሉ፡፡ ምልክቶቹም ከፍተኛ እልህ፤ አልታዘዝ ባይነት፤ ሌሎችን ተገቢ ባልሆነ ሁኔታ መውቀስ፤ በቀላሉ ማኩረፍ፤ ቁጠኛ እና በቀለኛ ከመሆን አንስቶ እስከ አብዝቶ ደጋግሞ መዋሸት፤ ጠብ አጫሪ መሆን፤ ለእንስሳትም ሆነ ለሰዎች ርህራሄ አልባ መሆን፤ ስርቆት፤አጥፊነት የወሲብ ጥቃት መፈፀም ወዘተ…. ሊጠቀሱ የሚችሉ መሆናቸውም ተካትቷል፡፡ በአጠቃላይ በባህሪ ቀውስ ውስጥ ያሉ ወጣቶች የቤተሰብ የትምህርት ቤትና የማህበረሰብን ደንብ ባለማክበር ከአካባቢ ጋር ከመጋጨት ባሻገር ህግን በመጣስ በተደጋጋሚ በህግ ጥበቃና ቁጥጥር እስከ መሆን ይደርሳሉ፡፡
4 ትምህርት የመከታተል ችግር
ወጣቶች ትምህርታቸውን መከታተል ሲያቅታቸው ወላጆች ለጭንቀት ያዳረጋሉ፡፡ ተማሪዎች በትምህርታቸው ከሚደክሙባቸው ምክንያቶች አንዱ የመከታተል ችግር መከሰት ነው፡፡ እንደ ጥናቱ ምልከታ በተለይ ምንም አይነት የአእምሮ ዝግመትም ሆነ የአእምሮ መቃዎስ እንዲሁም የጠባይ መቃወስ በሌለበት ሁኔታ ከሆነ የመከታተል ችግር ሊሆን ስለሚችል ወላጆችም ሆኑ መምህራን ልዩ ትኩረት ሊሰጡት እንደሚገባ ያትታል፡፡
5 የወጣቶች ሱስ አምጪ ተጠቃሚነት
ህፃናት ወደ ወጣትነት እድሜ ሲገቡ ቀስበቀስ ከአሳዳጊዎች ቁጥጥር በመውጣት ነፃነታቸውን ስራ ላይ ማዋል ይጀምራሉ፡፡ በዚህ ጊዜ ከህፃንነታቸው ጀምሮ ሌሎች ሲያደርጉት ያዩትን እነሱም ለመሞከር ይወስናሉ፡፡ ጎጅ የሆኑትም ድርጊቶች የሙከራው መነሻ ይሆናሉ፡፡ ከዚህም ውስጥ ሱስ አምጭ ጎጅ ነገሮች ማለትም ሲጋራ፤ጫት፤ አልኮል መጠጦች፤ የሚሸተቱና በተለያየ መንገድ የሚወሰዱ እፆችና መድሃኒቶች ይገኙበታል፡፡ለአንዳንድ ወጣቶች የሚወስዱት እፅ ለአእምሮ አለመረጋጋታቸው እንደ መፍትሄ የሚወሰዱ እርምጃዎች ሲሆኑ ሌሎቹ ደግሞ ከወላጆቻቸው የተማሩት አለበለዚያም ራሳቸውን ከመሰል ወጣቶችና አዋቂዎች ተርታ የሚያሰልፉበት መንገድ አድርገው ስለሚያስቡ ነው፡፡
በወጣቶች የሚከሰት የሱስ አምጭ ነገሮች ተጠቃሚነት ለተለያዩ ከፍተኛ አደጋዎች ያጋልጣል፡፡ የተለያዩ አካላዊ አደጋዎች/ወንጀሎች ያልተፈለገ እርግዝና፤ ኤች አይ ቪ ኤድስን ጨምሮ የተለያዩ በወሲብ የሚተላለፉ በሽታዎች እና ለራስ ማጥፋት ድርጊት እንደሚያጋልጡ አለማቀፍ ጥናቶች ያስገነዝባሉ፡፡
6 በወጣትነት የሚከሰት የራስ ማጥፋት ድርጊት
ራስ ማጥፋት የወጣቶችን ህይወት በማሳጠር በአለም በ3ኛ ደረጃ ላይ ይገኛል፡፡
አብዛኞቹ ህይወታቸውን የሚያጠፉ ወጣቶች በተለያየ የአእምሮ ጤና ቀውስ ውስጥ ይገኛሉ፡፡ በዓለም በየአመቱ ቢያንስ 4 ሚሊዮን ወጣቶች ራስ የማጥፋት ሙከራ ያደርጋሉ፡፡ ከዚህ ውስጥ ቢያንስ 100000 የሚሆኑት በተያያዘ ድርጊት ይሞታሉ፡፡ በምዕራቡ አለም ራስን ማጥፋት ከድብርትና ሌሎች የአእምሮና የባህሪ ችግሮች ጋር የተያያዘ ሲሆን በማደግ ላይ ባሉ አገሮች ደግሞ ከላይ በተጠቀሰው በተጨማሪ ከማህበራዊና ፖለቲካዎ አለመረጋጋት እንዲሁም ከድህነትና ከሃይማኖት ጋር በአብዛኛው እንደሚያያዝ ጥናቶች ያመለክታሉ፡፡
ወጣቱ ራሱን ለመጉዳት አደጋ ላይ እንደሚሆን ጠቋሚ ምልክቶች መካከል
– የአመጋገብና እንቅልፍ ስርዓት መዛባት
– ቤተሰብ፤ጓደኞችና የዕለት ተዕለት እንቅስቃሴ መገለል
– ከቤት መጥፋት ያልተለመደ ዐመፀኛ ጠባይ
– የአልኮልና ሱስ አምጭ ነገሮች ተጠቂ መሆን
– ባልተለመደ ሁኔታ ራስን መጣል
– ስልቹነት፤አእምሮን ማሰባሰብ አለመቻል
– የተለያዩ ምክንያ የለሽ አካላዊ ችግሮች ለምሳሌ ሆድ ህመም፤ ራስ ህመም፤ ድካም ወዘተ….
– ለምንም ነገር ስሜት አልባ መሆን፤ወዘተ… ለአብነት የተጠቀሱ ከፍተኛ የአእምሮና የባህሪ ችግሮች ናቸው፡፡
ከመከላከልና ህክምናው ውስጥም ህፃናት ገና ከመወለዳቸው በፊት ጀምሮ ወላጆች እርግዝናውን በማቀድ ከዚያም ለ ፅንሱ ተገቢውን እንክብካቤ ማትም የእናቲቱን አካላዊና አዕምሯዊ ጤና የተሟላ ማድረግ በወሊድም ወቅት ተያያዥ ችግሮች እንዳይከሰቱ ጥንቃቄ ማድረግ ለህፃኑ የተሟላ የአካልና የአእምሮ ጤና ከፍተኛ አወንታዊ አስተዋፅኦ አለው፡፡ በህፃንነት የሚደረግ የተሟላ እንክብካቤ ወደ ወጣትነት የሚደረገው ሽግግር የተስተካከለ እንዲሆን ያደርጋል፡፡ የተስተካከለ አመጋገብ የተረጋጋና የተሟላ ቤተሰብና አካባቢ ከተለያዩ ወረርሽኝና ቅፅበታዊ በሽታዎች መጠበቅ በአካል በተለይም በራስ ቅል ከሚደርሱ አደጋዎች ታዳጊውን መጠበቅ እንዲሁም አዎንታዊ የጤና አስተዋፅኦ ሲኖረው በየወቅቱ ቤተሰብና ማህበረሰብ የወጣቱን የተናጥልና የድምር ፍላጎት በሚገባ በመመርመር ከጎጅ.ልማዳዊ ድርጊቶች በማራቅ ጠቃሚ ባህላዊና ዘመናዊ እሴቶችን በማዳበር ተገቢውን እንክብካቤ ማድረግ አስፈላጊ መሆኑ በጥናቱ ተብራርቷል፡፡

1 ከፍተኛ ጭንቀ

ነፃነት ከባድ ነው! ስነ ልቦናዊ ምክኒያቶቹ

ብዙ ለነፃነት የታገሉ ሰዎች ከነፃነት በኃላ ጨቋኝ ይሆናሉ፡፡ ከነፃነት በኃላ በሚፈጠሩ ትርምሶችም ምክኒያት ብዙዎች “ጭቆናው ይሻለን ነበር!” ሲሉም ይሰማል፡፡ “የግብፅ ሽንኩርት ይሻለን ነበር!” አይነት ጉርምርምታም፡፡ ማህበራዊ ሚዲያዎች ነፃ ሲሆኑ ጉዳታቸው የሚያመዝንባቸው ጊዜያት አለ። ነፃነት ግን ለምን ከባድ ሆነ? ስነ ልቦናዊ ምክኒያቶቹ፦

1) በብዛት ነፃነት ፍለጋ የሚደረጉ እንቅስቃሴዎች ‘ነፃ መውጣት’ እንጂ ነፃ ሆኖ ምን ማድረግ የሚለው ላይ አያተኩሩም፡፡ ከሱስ ነፃ መሆን የሚለው እንጂ ምን መስራት የሚለው አይታሰብም፡፡ “ከዚህ ትዳር/የፍቅር ግንኙነት ነፃ መውጣት” የሚለው እንጂ ከዛስ ምን መሆን የሚለው አይጠየቅም፡፡ አሜሪካ መሄድ እንጂ ሄጄ ምን አደርጋለሁ የሚለው አይመዘንም፡፡(አሜሪካ በጣም ነፃ ሀገር ናት በሚል ነው፡፡)ጨቋኝ ስርአትን መለወጥ እንጂ እንዴት እመራለሁ አይታሰብም፡፡ ባጠቃላይ ነፃ መውጣት እንጂ ወደ ምን መግባት የሚለው አይታሰብበትም፡፡It is “freedom from” not “freedom to”

2) ነፃነት ግራ ያጋባል፡፡ አብዛኛው ማህበራዊ ግንኙነታችን መሪና ተከታይ ያለው እንጂ በነፃ ምርጫ ላይ የተመሰረተ አይደለም፡፡ ሰዎች በቡድን ስንሆን መሪና ተመሪ ይፈጠራል፡፡ የመገዛት ናፍቆት ያላቸው ብዙሀን እና የስልጣን ጉጉት ያላቸው ጥቂቶች አሉ፡፡ (ሁለቱንም የማይፈልግ አርቲስትም አይጠፋም፡፡) የሚወስነው ካልወሰነ ወይም የሚከተለው ካልፈቀደ ግራ መጋባት ይፈጥራል፡፡ አእምሮ ውጤቱ አጠራጣሪ በሆነ መልኩ ጥሩ ሊሆን ከሚችል ሁኔታ በእርግጠኝነት የሚታወቅ መጥፎ ሁኔታን ይመርጣል፡፡ የሚፈጥረውን ግራ መጋባት ለመቀነስ ወደ ተለመደው አካሄድ ማዘንበል፡፡ ከነፃነት በኃላ የተገዢነት ናፍቆት ወይም የስልጣን ጉጉት አንዱ ምንጭ ግራ መጋባትን ለመቀነስ ነው፡፡

3) ነፃነት ያስፈራል፡፡ ነፃነት ሁኔታን በግለሰብ ደረጃ መዝኖ ምላሽ መስጠት ነው፡፡ በግለሰብ ደረጃ የሚወሰን ከሆነ ሀላፊነት ተከትሎት ይመጣል፡፡ በግለሰብ ደረጃ መወሰን ማለት ከቡድን መለየት ስለሆነ የብቸኝነትና የትንሽነት ስሜት ይፈጥራል፡፡ ይህንን ስሜት ጠንክሮ ማለፍ ካልተቻለ አስፈሪ ነው፡፡ በቡድን ውስጥ ደህንነት አለ፡፡ ምንም እንኳን ለደህንነት የሚከፈለው ዋጋ ነፃነት ቢሆንም፡፡ በቡድን ውስጥ ስምም ሀላፊነትም የለም፡፡ በቡድን ድንጋይ ይዞ የመጣው “ከእናንተ ሀጢያት የሌለበት የመጀመሪያውን ድንጋይ ይወርውር።” ተብሎ በግለሰብ ደረጃ ሀላፊነት ሲሰጠው ወደመጣበት መመለሱ አይቀርም፡፡ ነፃነትን ከማንኛውም የቡድን ትስስር እንደመላቀቅ ካየነው ከሞቀው እና ደህንነት ካለበት የቡድን ማህፀን የሚያስተሳስረን እትብት ሲቆረጥ እናለቅሳለን እንጂ አንደሰትም፡፡
የታሰርንባቸው ገመዶች እየቆረጥን ነፃ ስንሆን የሚያስፈራ የትንሽነትና የብቸኝነት ስሜት ይሰማናል፡፡ ከዚህ ስሜት ለመላቀቅ ነፃነትን አስረክቦ መረጋጋት ይቻላል፡፡ የተሻለው መፍትሄ ግን በነፃነት ምክኒያት የሚመጣውን የትንሽነትና የብቸኝነት ስሜት በውጤታማ ስራና ቅድመ ሁኔታ በሌለው ፍቅር ማሸነፍ ነው፡፡

አብዛኞቹ ሀሳቦች ከ Erich Fromm “The Fear of Freedom” የተወሰዱ ናቸው፡፡

ነፃነት ማለት በሚፈቅዱት ሰንሰለት መታሰር ማለት ይሆን እንዴ?
መልካም ጊዜ!
ዶ/ር ዮናስ ላቀው

ትኩረት የሚሹ የወጣቶች ችግሮች ከሚለው ከባለፈው የቀጠለ.

5 የወጣቶች ሱስ አምጪ ተጠቃሚነት
ህፃናት ወደ ወጣትነት እድሜ ሲገቡ ቀስበቀስ ከአሳዳጊዎች ቁጥጥር በመውጣት ነፃነታቸውን ስራ ላይ ማዋል ይጀምራሉ፡፡ በዚህ ጊዜ ከህፃንነታቸው ጀምሮ ሌሎች ሲያደርጉት ያዩትን እነሱም ለመሞከር ይወስናሉ፡፡ ጎጅ የሆኑትም ድርጊቶች የሙከራው መነሻ ይሆናሉ፡፡ ከዚህም ውስጥ ሱስ አምጭ ጎጅ ነገሮች ማለትም ሲጋራ፤ጫት፤ አልኮል መጠጦች፤ የሚሸተቱና በተለያየ መንገድ የሚወሰዱ እፆችና መድሃኒቶች ይገኙበታል፡፡ለአንዳንድ ወጣቶች የሚወስዱት እፅ ለአእምሮ አለመረጋጋታቸው እንደ መፍትሄ የሚወሰዱ እርምጃዎች ሲሆኑ ሌሎቹ ደግሞ ከወላጆቻቸው የተማሩት አለበለዚያም ራሳቸውን ከመሰል ወጣቶችና አዋቂዎች ተርታ የሚያሰልፉበት መንገድ አድርገው ስለሚያስቡ ነው፡፡
በወጣቶች የሚከሰት የሱስ አምጭ ነገሮች ተጠቃሚነት ለተለያዩ ከፍተኛ አደጋዎች ያጋልጣል፡፡ የተለያዩ አካላዊ አደጋዎች/ወንጀሎች ያልተፈለገ እርግዝና፤ ኤች አይ ቪ ኤድስን ጨምሮ የተለያዩ በወሲብ የሚተላለፉ በሽታዎች እና ለራስ ማጥፋት ድርጊት እንደሚያጋልጡ አለማቀፍ ጥናቶች ያስገነዝባሉ፡፡
6 በወጣትነት የሚከሰት የራስ ማጥፋት ድርጊት
ራስ ማጥፋት የወጣቶችን ህይወት በማሳጠር በአለም በ3ኛ ደረጃ ላይ ይገኛል፡፡
አብዛኞቹ ህይወታቸውን የሚያጠፉ ወጣቶች በተለያየ የአእምሮ ጤና ቀውስ ውስጥ ይገኛሉ፡፡ በዓለም በየአመቱ ቢያንስ 4 ሚሊዮን ወጣቶች ራስ የማጥፋት ሙከራ ያደርጋሉ፡፡ ከዚህ ውስጥ ቢያንስ 100000 የሚሆኑት በተያያዘ ድርጊት ይሞታሉ፡፡ በምዕራቡ አለም ራስን ማጥፋት ከድብርትና ሌሎች የአእምሮና የባህሪ ችግሮች ጋር የተያያዘ ሲሆን በማደግ ላይ ባሉ አገሮች ደግሞ ከላይ በተጠቀሰው በተጨማሪ ከማህበራዊና ፖለቲካዎ አለመረጋጋት እንዲሁም ከድህነትና ከሃይማኖት ጋር በአብዛኛው እንደሚያያዝ ጥናቶች ያመለክታሉ፡፡
ወጣቱ ራሱን ለመጉዳት አደጋ ላይ እንደሚሆን ጠቋሚ ምልክቶች መካከል
የአመጋገብና እንቅልፍ ስርዓት መዛባት
ቤተሰብ፤ጓደኞችና የዕለት ተዕለት እንቅስቃሴ መገለል
ከቤት መጥፋት ያልተለመደ ዐመፀኛ ጠባይ
የአልኮልና ሱስ አምጭ ነገሮች ተጠቂ መሆን
ባልተለመደ ሁኔታ ራስን መጣል
ስልቹነት፤አእምሮን ማሰባሰብ አለመቻል
የተለያዩ ምክንያ የለሽ አካላዊ ችግሮች ለምሳሌ ሆድ ህመም፤ ራስ ህመም፤ ድካም ወዘተ….
ለምንም ነገር ስሜት አልባ መሆን፤ወዘተ… ለአብነት የተጠቀሱ ከፍተኛ የአእምሮና የባህሪ ችግሮች ናቸው፡፡
ከመከላከልና ህክምናው ውስጥም ህፃናት ገና ከመወለዳቸው በፊት ጀምሮ ወላጆች እርግዝናውን በማቀድ ከዚያም ለ ፅንሱ ተገቢውን እንክብካቤ ማትም የእናቲቱን አካላዊና አዕምሯዊ ጤና የተሟላ ማድረግ በወሊድም ወቅት ተያያዥ ችግሮች እንዳይከሰቱ ጥንቃቄ ማድረግ ለህፃኑ የተሟላ የአካልና የአእምሮ ጤና ከፍተኛ አወንታዊ አስተዋፅኦ አለው፡፡ በህፃንነት የሚደረግ የተሟላ እንክብካቤ ወደ ወጣትነት የሚደረገው ሽግግር የተስተካከለ እንዲሆን ያደርጋል፡፡ የተስተካከለ አመጋገብ የተረጋጋና የተሟላ ቤተሰብና አካባቢ ከተለያዩ ወረርሽኝና ቅፅበታዊ በሽታዎች መጠበቅ በአካል በተለይም በራስ ቅል ከሚደርሱ አደጋዎች ታዳጊውን መጠበቅ እንዲሁም አዎንታዊ የጤና አስተዋፅኦ ሲኖረው በየወቅቱ ቤተሰብና ማህበረሰብ የወጣቱን የተናጥልና የድምር ፍላጎት በሚገባ በመመርመር ከጎጅ.ልማዳዊ ድርጊቶች በማራቅ ጠቃሚ ባህላዊና ዘመናዊ እሴቶችን በማዳበር ተገቢውን እንክብካቤ ማድረግ አስፈላጊ መሆኑ በጥናቱ ተብ

ትኩረት የሚሹ የወጣቶች ችግሮች
ጥናቶች እንደሚያመላክቱት ከዛሬ አስርት አመታት በፊት በአለም ላይ ካሉት ህፃናት ወጣቶች ውስጥ እስከ 20 በመቶ የሚሆኑ ልዩ ልዩ የባህሪ ችግሮች ያላቸው ሲሆኑ ከዚህ ውስጥ ከ3-4 በመቶ የሚሆኑ ህክምና የሚያስፈልጋቸው ናቸው፡፡
በህፃናትና ወጣቶች ላይ ከ10 መሪ የጤና ቀውስ ከሚያስከትሉት ምክንያቶች 5ቱ የባህሪይ እና የአእምሮ ጤና ችግሮች መሆናቸውን ጥናቶች ያረጋግጣሉ፡፡
የህጻናትና ወጣቶች አእምሮ በተለያ ሰው ሰራሽና ተፈጥሯዊ ችግሮች ሊናጋ ይችላል፡፡ ከዚህም ውስጥ ዋናዋናዎቹ ጦርነት፤ ርሃብ፤ ድህነት፤ የእናቶች አካላዊ፤ ስነልቦናዊና ኢኮኖሚያዊ ችግር፤ የህፃናት ሰብአዊ መብቶች የአለመረጋገጥ ወዘተ በህፃናት ብሎም በወጣቶች ስነ-ልቦናና አእምሮ ላይ ከፍተኛ አሉታዊ ተፅእኖ ያሳድራሉ፡፡
እድገቱን ያልጨረሰው የወጣቶች አእምሮ በተለያዩ ምክንያቶች ባጭሩ ሊቀጭ ይችላል፡፡ ለምሳሌ ራስን ማጥፋት በ3ኛ ደረጃ ላይ የሚገኝ የወጣቶች ሞት መንስኤ ነው፡፡ ሌላው ወጣቶችን ለከፋ የአእምሮ ችግር ከሚያጋልጡት አንዱ ለአደገኛ መድሃኒቶችና ሱስ አምጭ እፆች አለአግባብ አጠቃቀም መሆኑን እንዲሁ ጥናቶች ያትታሉ፡፡ከጦርነት፤ ከመፈናቀል ወዘተ የሚመጡት ከፍተኛ የስነልቦና ቀውሶችና የአእምሮ ህመሞች ወጣቶችለበሽታ መዳረግ ብቻ ሳይሆን ህብረተሰቡንም ወደከፋ የማህበረሰብ ቀውስ ሊከትቱት ይችላሉ፡፡ በተለይም ከላይ የተጠቀሱት ዋና ዋና ምክንያቶች ለዘመኑ አስከፊ የጤናና ማህበራዊ ቀውስ ምክንያት ለሆነው ኤች አይቪ ኤድስ አቀጣጣይ ነዳጅ ናቸው፡፡
ከዚህ በታች የተዘረዘሩት የተለየ ትኩረት ሊሰጣቸው የሚገባ ወዋና ወዋና የወጣቶች የባህሪና ጤና ችግሮች መሆናቸውን ፕ/ር መስፍን አርአያ በ1996 ዓ.ም የስነ አእምሮ ጤና ቀንን ምክንያት በማድረግ በአቀረቡት አውደ ጥናት ላይ አመላክተዋል፡፡
1 ከፍተኛ ጭንቀት(Anxiety disorder)
2 ድብርት (Depressive disorder)
3 የብህሪ ቀውስ (Disruptive behavior disorder)
4 የመማር ቀውስ (Learning Disability)
5 የሱስ አምጭ ንጥረ ነገሮች አለአግባብ ተጠቃሚነት (Substance Abuse)
6 በወጣት ላይ የሚከሰት ራስ ማጥፋት (Teen Suicide)
የወጣቶች የአእምሮ ጤና ከወላጆች የአካል፤ የአእምሮና ማህበራዊ ደህንነት መረጋጋት ጋር በእጅጉ እንዲሚያያዝም በአውደ ጥናቱ ተመላክቷል፡፡ ሁለቱም ወላጆች እርስበርስ በመፋቀር በመከባበርና አርአያነት በአለው አኳኋን በመተሳሰብ በሚኖሩበት እቅፍ ውስጥ የሚያድግ ልጅ ይህ በአንድ ወይም በሌላ ምክንያት ባልተሟላበት ከሚያድግ ልጅ የተሻለ የአእምሮ እርጋታ እድገት እንደሚያሳይ ፕ/ር መስፍን በአቀረቡት ጥናት ላይ አመላክተዋል፡፡
1 ከፍተኛ ጭንቀት
ህጣናትና ወጣቶችን ከሚያጠቁ የአእምሮ ችግሮች አንዱ ከፍተኛ ጭንቀት ነው፡፡ በዚህ ችግር የሚሰቃዩ ወጣቶች ከፍተኛ ምክንያት አልባ ፍርሃት፤የልብ ምት መዛባት፤መበርገግ፤አእምሮን ማሰባሰብ አለመቻል በዚህም ምክንያት ትምህርትን በተገቢው ለመከታተል አለመቻል፤ መነጫነጭ፤ በተደጋጋሚና በቀጣይነት ለረጅም ጊዜ ሊታይባቸው እንደሚችል በጥናቱ ተዳሷል፡፡
2 ድብርት
ይህ የአእምሮ ጤና ችግር ብዙ ጊዜ በተለይ በህፃናት ላይ ሲከሰት አሳዳጊዎች ወይም መምህራን በቀላሉ ሳይገነዘቡት ለከፋ ሁኔታ የሚዳርግ ነው፡፡ ይህም የሚሆነው የህፃናቱ ወይም የወጣቶቹ ባህሪ ዝምተኛ ሲሆን ተቀባይነት ያለው ሆኖ ስለሚገኝ ነው፡፡ በአውደ ጥናቱ እንደቀረበው በተለይ አንድ ወጣት ቀድሞ ከነበረው ባህሪ እጅግ በተለየ ሁኔታ የእንቅልፍ፤ የመሳቅ፤ የመጫዎት፤ ወዘተ ባልተለመደ ሁኔታ ቀንሰው ከሆነ የጠባይ ቀውስ ለከሰቱ ይችላሉ፡፡ ምልክቶቹም ከፍተኛ እልህ፤ አልታዘዝ ባይነት፤ ሌሎችን ተገቢ ባልሆነ ሁኔታ መውቀስ፤ በቀላሉ ማኩረፍ፤ ቁጠኛ እና በቀለኛ ከመሆን አንስቶ እስከ አብዝቶ ደጋግሞ መዋሸት፤ ጠብ አጫሪ መሆን፤ ለእንስሳትም ሆነ ለሰዎች ርህራሄ አልባ መሆን፤ ስርቆት፤አጥፊነት የወሲብ ጥቃት መፈፀም ወዘተ…. ሊጠቀሱ የሚችሉ መሆናቸውም ተካትቷል፡፡ በአጠቃላይ በባህሪ ቀውስ ውስጥ ያሉ ወጣቶች የቤተሰብ የትምህርት ቤትና የማህበረሰብን ደንብ ባለማክበር ከአካባቢ ጋር ከመጋጨት ባሻገር ህግን በመጣስ በተደጋጋሚ በህግ ጥበቃና ቁጥጥር እስከ መሆን ይደርሳሉ፡፡
4 ትምህርት የመከታተል ችግር
ወጣቶች ትምህርታቸውን መከታተል ሲያቅታቸው ወላጆች ለጭንቀት ያዳረጋሉ፡፡ ተማሪዎች በትምህርታቸው ከሚደክሙባቸው ምክንያቶች አንዱ የመከታተል ችግር መከሰት ነው ።እንደ ጥናቱ ምልከታ … ይቀጥላል

Language/ቋንቋ